Ethiopia Declares National Mourning for Landslide Victims; Death Toll Hits 72

admin

Awramba Times is a US based online journal providing up-to-date news and analysis about Ethiopia email us: editor@awrambatimes.com

You may also like...

13 Responses

 1. dergu temelese says:

  የተለያየ ሽፋን ተጠቅሞ በትግራይ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተቀባይነት ስለሌለው፣ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አጥብቆ ይቃወመዋል፣ ይኮንነዋል። የት.ህ.ዴ.ን ድርጅት ለህዝብ ብሎ ከባድ መስዋዕት እየከፈለ ያለ ህዝባዊ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተቃራኒ የታጠቁ ሃይሎችን በህዝብ ላይ መጥፎ እርምጃ የሚወስዱ ሰወችን ደግሞ ከስርዓቱ ለይቶ እንደማያያቸው ያስጠነቅቃል። ስለዚህ ሁላችን ኢትዮጵያውያን ከጠባብነትና ከትምክህት ወጥተን የትግላችን ኢላማ በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ላይ ብቻ ማነጣጠር እንዳለበት ት.ህ.ዴ.ን ጥሪውን ያቀርባል።

 2. dergu temelese says:

  ታሪክህ ባጭሩ “ቆሼ ላይ ትወለዳለህ፤ ቆሼ ላይ ታድጋለህ፤ ቆሼ ላይ ትሞታለህ”

  [Atnaf Brhane]

  ቀን ጥሎህ ቆሻሻ ከሚምስ ትወለዳለህ፤ ቆሻሻ ላይ ዳዴ እያልክ ያገኘኸውን ወደ አፍህ እየከተትክ እድሜህ ለትምህርት ይደርሳል፤ እናትህ ቆሼ ጭራ ያገኘችውን ቋጥራ ትምህርት ቤት ትልክሃለች፤ አብረውህ የሚማሩ ልጆች “የቆሼ ሰፈር ልጅ” እያሉ ይሳለቁብሃል። ከትምህርት ቤት ስትመለስ ከእናትህ ጋር ለራት የሚሆን ምግብ ለመፈለግ የቆሼውን ክምር ትጭራለህ፤ እድለኛ ከሆንክ የተጣለ ምግብ ታገኛለህ።

  ሶስተኛ ክፍል ስትደርስ ስለ “ጀርም” ትማራለህ። ስትመገብ የኖርከው፣ ያደክበት ምግብ የተበከለ መርዝ መሆኑን ሳይንስ አስተማሪህ ይነግርሃል። ምንም አይመስልህም፤ አሞህ አያውቅማ፤ ሳይንስን ትጠራጠራለህ። ቆሼው አይጨክንብህም ያለውን ይሰጥሃል።

  አንተም ታድጋለህ፤ እናትህም ይደክማታል። ቆሼ ጭሮ ቤተሰብ የመመገብ ሐላፊነት ያንተ ይሆናል። ትምህርትህን ታቋርጥና ውሎህ የቆሼው ክምር ላይ ይሆናል። ኑሮ ያስጠላሃል፤ ትደበራለህ፣ ቁሩ ማጨስ፤ ጫት መገረብ ትጀምራለህ። የቆሼው ቦታ ሊቀየር መሆኑን ስትሰማ ህይወት ትጨልምብሃለች። ማን አለህ ያለ ቆሼ?! ማንም ዞር ብሎ አያይህም። መፈጠርህን የሚያውቅ የለም።

  በኑሮህ ሲመጡብህ ስጋት ይወርሃል። ደካም እናትህን ምን ታረጋታለህ? ዘርፈህ እንዳታበላት ባትዘርፍም ተጠርጣሪ ነህ። ማንም ከሰው አይቆጥርህም። ምርጫ ሲኖር ትዝ ትላቸዋለህ፤ ቆሼው ስር የወጠርካትን ሸራ ገልጠው ድምፅህ እንደሚያስፈልግ ይነግሩሃል፤ በየስብሰባው እየጠሩ 50 ብር እየሰጡ ሊያታልሉህ ሲሞክሩ እንዳላወቀ ሆነህ ታልፋቸዋለህ፣ 50ብሩ ይጠቅምሃላ፤ ደግሞም ደንቦች መጥተው ቆሼው ስር የወጠርካትን ሸራ ቢያፈርሱብህስ? የት መግቢያ አለህ? የትም!

  ከቆሼው ውጪ ሁሉም ጠላትህ ነው። የተመረዘው ምግብ ብቻ ነው ላንተ የሚራራልህ። አንድ ቀን ማታ ከቆሼ ያገኘኸውን ኡፋ ከናትህ ጋር ተቋድሰህ ስትተኛ ሁሉም ነገር በዛው ይጨልማል።
  አስቀይሞህ የማያውቀው ቆሼ በመጨረሻ ፊቱን ያዞርብሃል፤ ከእናትህ ጋር አፍኖ ይገልሃል።

  ሰው ነህ ግን ከተቆለለው ተራራ ከሚያክለው ቆሼ ታንሳለህ። ታሪክህ ባጭሩ
  “ቆሼ ላይ ትወለዳለህ፤ ቆሼ ላይ ታድጋለህ፤ ቆሼ ላይ ትሞታለህ” አለቀ!!

 3. dergu temelese says:

  የቆሻሻ ፖለቲካ ተምሳሌት – ቆሼ!! “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው”የግፍ ክምር ናዳው ምን ያህል የሚከፋ ይሆን?
  አዲስ አበባ ቃላት የማይገልጹዋት፤ ስሟ ግብሯን የማይወክል የግፍ ከተማ ናት፡፡ በአንድ በኩል ሥጋ በል ለሆኑ የቤት እንሰሳዎቻቸው የዕለት ተዕለት ምግብ ከሱፐርማርኬት የታሸገ ሥጋ ገዝተው የሚመግቡ ባለጠጎች፤ በሚስታቸውና በልጆቻቸው እንዲሁም በደርዘን ውሽሞቻቸው ሥም የተንጣለሉ ቪላ ቤቶችንና ግዙፍ ህንፃዎችን የገነቡ የገዥው ኃይል ማኅበራዊ መሰረት የሆኑ የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ የከተማ ዘራፊዎች (Marauders’ city) “ወጋ ትበለይኪ” እያሉ የሚምነሸነሹባት፤ ደሃ-ገፊ መሐል አሟቂ፤ የቁስ ሰቀቀን የተጫናቸው የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ዘዋሪ ልሒቃን ከተማ ናት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዕለት ምግባቸውን ከቆሻሻ ገንዳ የሚለቅሙ አንጀታቸው በረሃብ የታጠፈ ጐስቋላ ምንዱባን በጐዳና የሚኖሩባት፤ የወር ደመወዛቸውን ለአልቦ-አንጀት (ርህራሄ የለሽ!) አከራዮቻቸው እያስረከቡ ፓስቲ በልተው የረጋ ዘይት የሚያገሱ የኢኮኖሚ ምርኮኛ የመንግስትና የግል ሠራተኞች የሰቀቀን ሕይወት የሚገፉባት፤ ቆሻሻና ሰው ላይና ታች ሆኖ የሚኖርባት ጉራማይሌ ከተማ ናት – አዲስ አበባ!!
  ማህበራዊ መሰንጠቋ (Social Division) ገሃድ የወጣባት፤ የመደብ ልዩነቱ ለንፅፅር በማይመች ልዩነት ውስጥ ያለባት፤ በደሃ ደቋሽ አገዛዝ የተረገጠች፤ ድኾችን ወደ ጥግ የገፋች፤ አግላይ-ነጣይ የግፍ ከተማ!! አዲስ አበባ፡፡
  ህይወት በ“ቆሼ”
  በደቡብ ምዕራብ የከተማዋ አቅጣጫ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ “ቆሼ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ፤ ህይወት እንደሌላው አካባቢ “ቀላል” አይደለችም፡፡ እዚያ ቦታ ለመኖር አፍንጫን ከሚከረፋ፣ ልብን ከሚያጥለወልው ኃይለኛ የቆሻሻ ሽታ ጋር መስማማት ግድ ይላል፡፡ ቆሼን እንኳን ኑረውበት በመኪና መስኮት ከፍቶ አንድ አፍታ ሲያልፉበት ሽታው መፈጠርን ያስጠላል፡፡
  ቆሼ ውስጥ ግን ወገን አለ!! የተገፋ ወደ ዳር የተጣለ፤ በፖሊሲ አውጪዎች ሆን ተብሎ የተዘነጋ ኢትዮጵያዊ ወገን አለ፡፡ አንዳች ተስፋ በማይታይበት የቆሼ ቆሻሻ ክምር ግርጌ ነገን ተስፋ አድርጐ፤ ከሚከረፋው የቆየው ሽታ ባሻገር ውል የሚል መልካም መዓዛ እያለመ በቆሻሻ አገዛዝ የተገፋ፤ በቆሻሻ ፖለቲካ ከቀን ወደ ግራ የሚላተም፤ ቆሻሻ ግርጌ የሚተኛ ኢትዮጵያዊ ወገን አለ!!
  አዙሪት ሆነና ቆሼና አካባቢው በሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችም “የመደብ” ልዩነት ይታያል፡፡ ቆሼ አካባቢ ህጋዊ የመሬት ይዞታ ኖሯቸው በምሪት፣ በግዥ፣ . . . መኖሪያ ቤት ሰርተው ቤትም እያከራዩ የሚኖሩ ዜጐች ከሰው ሰራሹ ተራራ (ለዓመታት የተከማቸ የቆሻሻ ክምር) በቅርብ ርቀት ይኖራሉ፡፡ በአንፃሩ ተራራው ግርጌ ሥር የሚኖሩት ደግሞ የመሬት ይዞታቸው ያልተረጋገጠላቸው “የጨረቃ ቤቶች” ናቸው፡፡ በላስቲክ እንደነገሩ የተሰሩ “መኖሪያ ቤቶች”ም በሰው ሰራሹ ተራራ የቆሻሻ ክምር ዙሪያ ገባ ተኮልኩለዋል፡፡ እነዚህኞቹ ቤቶች ለቆሻሻ ክምሩ እጅግ ቅርብ ናቸው፡፡ የቤቶቹ ጥግግትም የተቃቀፉ በሚል የሚገለፅ ነው፡፡ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የከተማ አስተዳደሩ “ህገ-ወጥ የቤቶች ግንባታ” በሚል የድሆችን ቤት ማፍረስ በመያያዙ ከከተማዉ እየተገፉ ጥግ ላይ የሚከማቹ ነዋሪዎች በዝተዋል፡፡ ቆሼም ነዋሪዎችን በብዛት ከሚቀበሉ የአዲስ አበባ ዳርቻ ሰፈሮች አንዷ ናት፡፡ በቆሼ አካባቢ ሁሉም ችግረኛ የቻለ በአጣና ያልሆነለት በላስቲክ ጎጆ ቀልሶ የሚኖርባት የአዲስ አበባ ካልካታ ነች!!
  ሰው ሰራሹ ተራራ ባለፉት ስልሳ ዓመታት የአዲስ አበባ ቆሻሻ በአብዛኛው እዚህ ቦታ በመከማቸቱ የተፈጠረ የቆሻሻ ክምር ነው፡፡ በጊዜ ሂደትም መሬት በሚገባ ያልቆነጠጠ ግን ግዙፍ ሰው ሰራሽ ተራራ ሆኗል፡፡ የመልከዓ ምድር ሳይንስ እንደሚገግረን ተራሮች የሚፈጠሩት በመሬት መተጣጠፍ (እሳተ ጎመራ – volcanic eruption) ነው፡፡ የተራራ ናዳ ሊፈጠር የሚችለውም ከፍ ባለ የተፈጥሮ ኃይል ግፊት እንጅ እንዲህ በዋዛ አይደለም፡፡
  የቆሼ ሰው ሰራሽ ተራራ አፈጣጠር ግን ከዚህ ፍፁም የተለየ ነው፡፡ ተራራው ለተራዛሚ አመታት በከተማቸ ቆሻሻ (መርጋት) የተፈጠረ፤ አስተማማኝ የሚባል መሰረት የሌለው ተራራ መሰል የቆሻሻ ክምር ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ይህ ሰው ሰራሽ ተራራ በዝናብ እየተሸረሸረ በሄደ ቁጥር ከመሬት ጋር ያለው መጣበቅ እየላላ መሄዱ አይቀርም፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ ከዚህ ተራራ ጀርባ ያለውን ቦታ ለተጨማሪ የከተማው ቆሻሻ ማከማቻ በሚል የቅርብ ጊዜውን ቆሻሻ ወደ ነባሩ የቆሻሻ ክምር (ተራራ) በጀርባ በኩል በዶዘር እየታፈሰ ይጨመርበት ጀምሯል፡፡ የናዳው መንስኤም ይኸው ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ቢኖሩም የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በአካባቢዉ የሰፈሩትን ድሆች ነቅሎ የሚጥልበት ዘዴ ሲያሰላስል መክረሙን የሚናገሩም አሉ፡፡ እንደነዚህኞቹ አስተያየት ሰጪዎች ህዳርና ታህሳስ ወር/2009 ዓ.ም ላይ በተደጋገሚ የሚመላለሱ የከተማዋ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎች እንደነበሩ ያስታዉሳሉ፡፡ በጊዜ ሂደት ሰዉ ሰራሽ ተራራ ከሆነዉ የቆሻሻ ክምር ጀርባ ግልጽ ያልሆነ “የጥናት” ተግባር ላይ ተጠምደዉ የመክረማቸዉ ምስጢር ከአደጋዉ በኋላ ለአካባቢዉ ነዋሪዎች የተገለጠላቸዉ ይመስላል፡፡
  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ አወጣሁበት ያለውን የቆሻሻ መጣያ ስፍራ በሰንዳፋ አካባቢ ቢያስገነባም፤ የአካባቢው ገበሬዎች የከረረ ተቃውሞ በማንሳታቸው ችግር ውስጥ የገባው የከተማ አስተዳደር፤ የከተማዋን የቆሻሻ መጣያ (ቆሼን) የሙጥኝ ማለቱን ገፋበት፡፡ በዚህም የተበታተነውን ቆሻሻ በቀደመው ጊዜ ሰው ሰራሽ ተራራ ከሰራው ክምር ቆሻሻ ጋር በጀርባ በኩል (በፊት ለፊት ሜዳና አባጣ ጐርባጣ ሆኖ የመኖሪያ ቤቶች መኖራቸውን ያስታውሷል) በዶዘር እየገፋ መጨመሩን እና ከኋላ በኩል ገላጣ ቦታ ማስፋቱን ቀጠለበት፡፡ በዚህ ሂደት ነባሩ ሰው ሰራሽ ተራራ መሬትን ቆንጥጦ የያዘ ባለመሆኑ፤ ከዚህ ባለፈ በዝናብ አፈሩ እየተሸረሸረ የመጣ በመሆኑ የቆሻሻው ክምር ከተራራው ግርጌ ወደ ተከለከሉ ቤቶች በናዳ መልኩ ለመውረድ ጊዜውን እየጠበቀ ነበር፡፡ በተለይም ከቆሻሻ ክምሩ ተራራ ጀርባ በዶዘር ተጨማሪ ቆሻሻ እንዲቆለልና ነባሩ የቆሻሻ ክምር ለወራት ያህል እንዲነካካ መደረጉ የጉዳዩን ሤራ ግልጽ ያደርገዋል፡፡
  ህይወት በቆሼ ጉራማይሌ ናት፡፡ የላስቲክ ቤቶች፣ በጨፈቃ/አጣና እንደነገሩ የተሰሩ ቤቶች፣ የእንጨት ቤቶች፣ ግቢ ቤቶች ራቅ እያሉ ሲሄዱ ደግሞ የብሎኬት ቤቶችም አሉ፡፡ ወደ ቆሻሻው ክምር እየቀረቡ ሲሄዱ የቤቶች ጥግግት ከላይ እንደገለጽነው ከመደጋገፍ በተጨማሪ አስተቃቅፏቸዋል፡፡ የቆሼ ክምር ቆሻሻ ሽታ በቦታ ቅርበትና ርቀት መጠኑ ቢለያይም የቆሻሻው ሽታ እስከ አምስት መቶ ሜትር ርቀት ድረስ ያካልላል፡፡
  ቆሼ ለተገፉት ድሆች መርካቶም ቦሌም ነች፡፡ ምግብም ብርም የሚለቀምባት፡፡ “ምግብ” የሚባለው በዕለት ተዕለት ቆሻሻ መጣያው (ከነባሩ ሰው ሰራሽ የቆሻሻ ክምር ጀርባ ባለው ቦታ) በየዕለቱ የሚደፋውን ቆሻሻ በመፈለስ የሆቴሎችን ትርፍራፊ ምግብ፣ ከአትክልት ቤቶች ተበላሽተው የሚጣሉ ፍራፍሬዎችንና መሰል “ምግብ” ነክ ነገሮችን ያጠቃልላል፡፡ በቆሼ ብርም ይለቀማል ሲባል ደግሞ የተቆራረጡ ብረታ ብረቶችን፣ ቆርቆሮዎችን በመልቀም፤ ያገለገሉ የውሃ ፕላስቲኮችን በመሰብሰብ፤ ከቆሻሻ ጋር የሚጣሉ አልባሳትን በመፈለግ፤ የቅባት ጠርሙሶችን፣ ጆንያዎችን፣ ያገለገሉ የማብሰያ ዕቃዎችን … ከቆሻሻው በመሰብሰብ እንዳቅሚቲ ወደ ገበያ በማውጣት ለሽያጭ ያቀርባሉ፡፡ በዚህ የዕለት ኑሯቸውን የሚገፉ፣ ትዳር የመሰረቱ፣ ወልደው የከበዱ ነዋሪዎች የቆሼ ቤተሰብ ናቸው፡፡ ቆሼ ተወልደው ቆሼ ያደጉ፤ ትምህርት ባይዘልቁም በቆሻሻ ክምር ውስጥ የተፈጠረን ሰው ሰራሽ ተራራን የዘለቁ፤ የቆሻሻ ክምር ሸለቆን ያካለሉ … የቆሼ ህይወት ያስተማራቸው ልጆች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡
  በቆሼ እየኖሩ ከሚጣለው ቆሻሻ ምግባቸውንና የገቢ ምንጫቸውን የሚያፈላልጉ ነዋሪዎች በላስቲክ ቤቶችና እንደነገሩ በሆኑ የአጣና/ጨፈቃ ቤቶች ከሰው ሰራሹ ተራራ ግርጌ ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ነዋሪዎች “ምግብ” ነክና አሮጌ አልባሳትና ያገለገሉ የቤት ዕቃዎችን ከቆሻሻ ቦታው ፈልገው የሚያገኙባቸው ዕለቶች እንዲሁም የብረታ ብረት ቁርጥራጮችን፣ ቆርቆሮዎችንና መሰል ቁሳቁሶችን ፈልገው የሚያገኙባቸው ዕለቶች የተለያዩ ናቸው፡፡ “ምግብ”፣ አሮጌ አልባሳትና ያገለገሉ የቤት ዕቃዎችን በአብዛኛው ሰኞ እና ማክሰኞ ከየአቅጣጫው ከሚመጡ ቆሻሻ ጫኝ መኪናዎች ቆሼ ላይ በሚደፋበት ጊዜ እንደ ንብ መንጋ መኪናዎቹን ወርረው “ምግቡንም”፣ አሮጌ አልባሳቱንም፣ ያገለገሉ የቤት ዕቃዎችንና የተገኘውን ነገር ከቆሻሻው እየፈለፈሉ በመሻማት ይለቅማሉ፡፡ ቅዳሜ እና እሁድ የሆቴሎችና የአትክልት ቤቶች የገበያ ሁኔታ ከሌሎች ዕለታት በአንፃሩ ተለይቶ ስለሚሟሟቅ ከልምድ በእነዚህ ዕለታት ወደ ቆሻሻ መጣያው በመኪና ተጭነው እንደሚመጡ የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ምንጮች ቦታው ድረስ ተገኝተው ያደረጉት ማጣራት ያመለክታል፡፡ ቅዳሜና እሁድ በሚጣሉ ቆሻሻዎች ውስጥ ደግሞ በአብዛኛው ሳምንቱን ሙሉ የተሰራባቸው የብረታ ብረት ቁርጥራጮች፣ የውሃ ፕላስቲክ ኮዳዎች፣ ቆርቆሮዎች፣ የፀጉር ቅባት ጠርሙሶችና፣ . . . ወዘተ ይገኛሉ፡፡ በበዓላት ማግስት የሚደፋ ቆሻሻ ክትፎና ጐድን ጥብስ፣ የፍየል እና የበግ ጭንቅላት፣ ጨጓራና ሌሎች የሆድ ዕቃ አካላት ፣ . . . የመሳሰሉ የ“ምግብ በረከቶች” ይገኛሉ፡፡ አንዳንዴም ጥቅም ላይ የዋለ ኮንዶምና የጫት ገረባ ከትርፍራፊ የሆቴል ምግቦች ጋር ተቀላቅሎ ይገኛል፡፡ ቆሼ እንዲህ ነች!! ለማመን የሚከብዱ ትዕይንቶች ዕለት በዕለት ሚስተናገዱባት የኢትዮጵያ እዉነተኛ ገጽታ!!
  አዲስ አበባ የግፍ ከተማ ነች የምንላትም ለዚህ ነው፡፡ ቆሼ ውስጥ “ምግብ” ፍለጋ ቆሻሻ የሚያገላብጥ ታዳጊ ህፃን በድንገት ጥቅም ላይ የዋለ ኮንዶም ከጫት ገረባ ጋር ቢያገኝ አይገርመውም፤ ይልቁንስ ጊዜው እንዳይባክን በባልንጀሮቹ እንዳይቀደም ቆሻሻውን ተጐንብሶ እየፈለሰ “ምግብ” አልያም ወደ ብር የሚቀይረው ቁሳቁስ መፈለጉን ይቀጥላል፡፡ . . . ህይወት በቆሼ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 02/2009 ዓ.ም. እንዲህ ቀጥላ ነበር፡፡
  የመዓቱ ምሽት…
  እኒህ በቆሻሻ አገዛዝ ተገፍተው ቆሻሻ ግርጌ ለመኖር የተገደዱ፤ ቆሻሻ እየለቀሙ በቆሻሻ ግርጌ ጐጆ ቀልሰው እንዲኖሩ ዕጣ ፋንታ የሆነባቸው የምድር ጐስቋሎች ከየአቅጣጫው የቀኑን የሰርክ ዘመቻ በድል አጠናቀው ወደየማደሪያ ጐጇቸው ከትተዋል፡፡ ቆሼ ግርጌ ቤት ሰርተው የመንግሥትና የግል ሰራተኛ የሆኑ የኢኮኖሚ ምርኮኞችም ወደየጐጆዎቻቸው መጠቃለል ጀምረዋል፡፡ በአካባቢው ውር ውር የሚሉም አልጠፉም፡፡ የቆሼ አካባቢ ውሾች ማላዘን በጀመሩበት የቅዳሜ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ የምድር ጐስቋሎቹ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የቆሼ ሰማይ ጠቀስ ሰው ሰራሽ ተራራ የቆሻሻ ክምር እንደብራ መብረቅ፣ እንደደራሽ ውሃ ሙላት በበላያቸው ላይ ተደፈነባቸው፡፡ የቆሻሻ ክምር እንደ ጐርፍ አካባቢውን አጥለቀለቀው፡፡ በአካባቢው የነበረ ሕይወት በቅፅበት ከመኖር ወደ አለመኖር ተቀየረ፡፡ አስር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የላስቲክ ቤቶቹን ሳይጨምር (እንደ አካባቢው ነዋሪዎች መረጃ ሃያ ስምንት የላስቲክ ቤቶች በናዳው ተደፍነዋል) ከሰላሳ ሰባት በላይ በእንጨት የተሰሩ መኖሪያ ቤቶች በቆሻሻ ክምር ናዳ ተዳፍነዋል፡፡ አባቶች ከነምርኩዛቸው፣ እናቶች ከነልጆቻቸው፣ ወጣቶች ከነህልማቸው ቆሻሻ ክምር ግርጌ እየኖሩ በቆሻሻ ናዳ እስከወዲያኛው አሸለቡ፡፡
  እንደ ጎልጉል የአካባቢው መረጃ ሰጪዎች “አደጋው በደረሰ ቅፅበት የአምቡላንስና የድንገተኛ አደጋ እርዳታ ሰጪ የህክምና ባለሙያዎች በፍጥነት ደርሰው ቢሆን ኑሮ፤ የቆሻሻውን ክምር ተጠግተው የተሰሩ ቤቶች ውሰጥ የነበሩ ሰዎችን ማዳን ባይቻል እንኳ ወደ ዳር አካባቢ (የናዳው የመጨረሻ የክምር እንክብል ያረፈባቸው) ቤቶች ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ማዳን ይቻል ነበር” ሲሉ አስተያየታቸውን ገልፀዋል፡፡
  “ብዙ ቤቶች ላይ አደጋ ደርሷል፣ ቤቶች ተደርምሰዋል . . . እያለ ህዝቡ እሪ ሲል እና በየአቅጣጫው ስልክ እየደወለ የድረሱልን ድምጽ እያሰማ በነበረበት ሁኔታ ፈጥና የመጣችው አንዲት የአለርት ሆስፒታል አምቡላንስ ብቻ ነበረች” በማለት በቦታው የነበረ የአይን እማኝ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ በአካባቢው ፈጥነው የደረሱት ናዳው ቤታቸውን ያልነካባቸው ሰዎች ቢሆኑም በድንጋጤ ደርቀው ከማየት ባሻገር እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል አቅም አልነበራቸውም፡፡
  “አደጋው ከደረሰ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ከአየር ጤና፣ ካራ ቆሬ፣ መካኒሳ፣ ዘነብ ወርቅና በአቅራቢያዉ ያሉ አካባቢዎች የሚኖረዉ ህዝብ ወደ ቆሼ ሰፈር መጉረፍ ቢጀምርም ናዳው የተከሰተበት ቦታ ሌላ ክምር የፈጠረ በመሆኑ ለፈጣን እርዳታ የሚያመች አልነበረም” የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ በናዳው የተነሳ የአካባቢው የኤሌክትሪክ መስመር የተቆራረጠ በመሆኑ የተፈጠረው ጨለማ ተጐጂዎችን ከተደፈኑበት ለማውጣት ተጨማሪ ፈተና ነበር፡፡
  ይህም ሆኖ ለጥንቃቄ በሚል የደረሱ የእሳት አደጋ መኪናዎች፣ የግለሰብ መኪናዎኖች፣ ዘግይተውም ቢሆን ቁጥራቸውን የጨመሩት አምቡላንሶች በርቀት በሚለቁት መብራትና የጨረቃ ብርሃን በመታገዝ ተጐጂዎችን ለማዳን ጥረት ቢደረግም ይህ ርብርብ ቅዳሜ ምሽት እስከ እኩለሌሊት ድረስ ብቻ ነበር የቆየው፡፡ ከዚህ በኋላ በነበሩት የሌሊት ሰዓታት አስከሬን ለማውጣትም ሆነ ተጐጂዎችን ለማፈላለግ የሚደረገው ሙከራ በይደር እንዲያዝ ከበላይ የአገዛዙ ኃላፊዎች ትዕዛዝ በመሰጠቱ ቆሟል፡፡
  ይሄው አስከሬን ፍለጋ ቅዳሜ ለእሁድ ንጋት 11፡00 ሰዓት ላይ እንደገና በአዲስ ኃይል በኤክስካቫተር ማሽኖችና በባለሙያዎች የተደገፈ ፍለጋ መካሄድ ጀመረ፡፡ “እጅግ አስቸጋሪው ነገር፤ የተደረመሰው የቆሻሻ ክምር ብዛት ከቤቶቹ ፍርስራሽ ጋር ተደምሮ ሌላ ግዙፍ ተራራ መፍጠሩና የቤቶቹን አቅጣጫ መለየት አለመቻሉ ነበር” የሚሉት የአካባቢው ወጣቶች “ፖሊስ ግራ በሚያጋባ መልኩ ከየአቅጣጫው ለእርዳታ የመጡ ሰዎች የአቅማቸውን ያህል “በአስከሬን ፍለጋው እንዳይተባበሩ ከልክሏል” በማለት በቦታው የነበረ አንድ ወጣት ስሜቱን እየገታ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ “የአስከሬን ፍለጋው በማሽንና በባለሙያ ብቻ ይካሄድ” የሚል አቋም ያላቸው ፖሊሶች ሁኔታውን እያወሳሰቡት እንደነበር የጎልጉል መረጃ ምንጭ በቦታው ተገኝቶ ታዝቧል፡፡
  እንደ አካባቢው የአይን እማኞች አደጋው ከደረሰበት ከቅዳሜ ምሽት 1፡00 ሠዓት ጀምሮ ባሉበት ስልሳ የፍለጋ ሰዓታት ውስጥ የሟቾች ቁጥር በተጨባጭ ሰማንያ ሦስት የደረሰ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በአለርት ሆስፒታልና በሌሎች የህክምና ተቋማት የሚገኙ የተጎጂዎችን ቁጥር የአገዛዙ የሚዲያ ልሳናት ስልሳ ሦስት ቢያደርሱትም ከተደፈኑ ቤቶች ብዛት አኳያ ቁጥሩ ከዚህ እጥፍ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ ሚዲያ በኩል የሟቾችን ቁጥር በዜና ዘገባ የማምታታት ሁኔታ በተደጋጋሚ እየታየ ነው፡፡
  ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሠዓት ድረስ የሟቾቹን አስከሬን መፈለጉ እንደቀጠለ ነው፡፡ ይሁንና በቁፋሮ የተገኙት አስከሬኖችን ማንነት መለየቱ ሌላ የአደጋው ፈታኝ ገጽታ ነው፡፡ ሰኞ ረፋድ ላይ በነበረው የአስከሬን ቁፋሮ ሂደት በኤክስካቫተር ማሽኖች እየተቆፈሩ ከወጡ የሟቾች አስከሬን ውስጥ የአራቱ አስከሬን ሆድ እቃቸው የተዘረገፈ፤ የሁለቱ ደግሞ ጭንቅላታቸዉ የደቀቀ መሆኑን ያዩ የአካባቢው ሀዘነተኞች በቦታው ለተገኘው የጎልጉል መረጃ አቀባይ ተናግረዋል፡፡
  እንደ ጎልጉል ዘጋቢ የአካባቢ ቅኝት ሪፖርት በዚህ ዘግናኝና አሰቃቂ አደጋ ውስጥ የታዩ እጅግ አሳዛኝ ክስተቶች በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው፡-
  በአንድ የቤት ውስጥ ሰባት የቤተሰብ አባላት ሙሉ በሙሉ አልቀዋል፤
  በቡድን ቁረዓን እየቀሩ ከነበሩ አምስት ታዳጊዎች ውስጥ ቁርዓን አስቀሪያቸውን ጨምሮ አንድም የተረፈ የለም፤
  ቤታቸው በናዳው ከተደረመሰባቸው የቆሼ ነዋሪዎች ውስጥ ሁለት ከአልጋ ላይ ያልወረዱ አራሶችና አንዲት የደረሰች ነፍሰ ጡር እናት እስከወዳኛው አሸልበዋል፤
  የሟቾችን ማንነት ለመለየት ያልተቻለበት ሁኔታ በመኖሩ በግምት በየቤተእምነቱ የተቀበሩ አሉ፤
  አብዛኛው ሟቾች ሴቶች፤ ህፃናት እና አረጋውያን ናቸው፤…
  ህወሃት/ኢህአዴግና ቆሻሻ
  የዜጎች ድህነት የሚያስደስተው ቆሻሻ አገዛዝ፤ ደሀ-ደቋሽ የሆኑ ፖሊሲዎቹ ውጤት የገዛ ዜጎቹን በቆሻሻ ክምር ናዳ መቅበር ሆኗል፡፡ አዲስ አበባ ማህበራዊ ስምምነት የራቃትና ማህበራዊ መሰንጠቋ በገሃድ የሚታይባት፤ ጥቂት ግፈኞች ብዙሃኑን መከረኛ ህዝብ በአግላይ-ነጣይ የማህበረ-ኢካኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፖሊሲዎቻቸው ረግጠው የሚገዙባት የግፍ ሞዴል ሆናለች፡፡
  ለከፋው ድህነት ቆሼና ገንዳዎች ባለውለታ ናቸው። ቆሼ ተንዶ ያኖራቸውንና አምነውት የተመሸጉበትን ዋጣቸው። ህወሃት የከመረውን የግፍ ናዳ ለሚያስቡ የቆሼ ናዳና ሃዘኑ የፈጠረው ስሜት ቀላል ነው። ንብረታቸውን እየተቀሙ፣ መሬታቸውን ህወሃቶች እየቸበቸቡባቸው ጎዳና የቀሩ፣ በገዛ ንብረታቸው ላይ ዘበኛና ታዛቢ የሆኑ፣ ለምን በማለታቸው የተገደሉ፣ የታሰሩ፣ “ቶርቸር” የተደረጉ፣ እንዲመከኑ የተደረጉ፣ ማንነታቸውን የተቀሙ፣ አገር እያላቸው አገር ያጡ፣ ባይተዋር የሆኑ፣ … እንደ ቆሼ አንድ ሰፈር ብቻ ሳይሆን በየቀበሌው የግፍ ቁልል ተራራ ሰርተዋል። ይህ ተራራ ሊናድ እየዳዳው በቋፍ ላይ ከሆነ ቆይቷል። ይህ የተናደ እለት. . . ከግፍ ተራራዎች ናዳ እንዴት እንተርፍ ይሆን?
  “ተሰዋ” የሚባለው፣ ነገር ግን በአንዳች ኃይል “ተንቀለ” የሚሉት መለስ “ዋናው ጠላታችን ድህነት ነው፤ በቀን ሶስቴ ትበላላችሁ፣ ድህነትን ታሪክ እናደርገዋለን” እያለ በስሩ ከሰበሰባቸው አስከሬኖች ጋር በመሆን የሚማማሉበት ህዝብ ማለት ይህ ነው። ፖለቲካውም ሆነ አገዛዙ ቆሻሻ የሆነውና ጥቂቶችን እያበለጸገ “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው” በማለት የሚቀልደው ህወሃት/ኢህአዴግ ለዓመታት በቆለለው ቆሻሻ መዋጡ አይቀሬ እንደሆነ ሁሉ ቆሼ ሰፈር ቆሻሻ ውስጥ ህይወት አቆይቶ መጨረሻው በቆሻሻ መዋጥ ሆኗል። ይህም ቢሆን እንኳን በቁማቸው ከሞቱ የባንዳ አገልጋዮች ይልቅ ቆሻሻ ይሻላል። ቆሻሻ መጨረሻ ላይ ጨከነ እንጂ መከለያ ሆኖ አኑሯል።
  የባሌ ተራሮችን ከሚመስሉ ሰው ሰራሽ የቆሻሻ ክምር ተራሮች ግርጌ የላስቲክ ቤቶችንና መጠነኛ የእንጨት ቤቶችን ሰርተው ለዓመታት አፍንጫ ከሚበጥስ ጠረን ጋር ተላምደው ኑራቸውን የሚገፉ ዜጎችን ችግር አይቶ እንዳላየ ያለፈ ቆሻሻ አገዛዝ፤ ልበ ንፁህ ዜጎችን ቆሻሻ ግርጌ ቀርቅሮ፤ በቆሻሻ ናዳ እንደቀበረ ታሪክ መዝግቦታል፡፡ ይህን የግፍ ታሪክ የሚፈርድ ጊዜና ትውልድ ደግሞ መምጣቱ አይቀርም፡፡ እስከዚያው ግን ጥልቅ ድህነት ቀስፎ የያዘን እኛ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሰው ሰራሽ የሞት አደጋዎች መተኪያ የሌላት ህይወታችንን ማጣታችን እንቀጥላለን. . .
  “ልጄ! ‘ሀገር ማለት ሰው ነው’ ያሉህን ተቀበል
  ሰው በሞተ ቁጥር ፣ ‘ሀገሬ ሞተች’ በል!!” (ግጥም – በላይ በቀለ ወያ)

 4. Megartu Begna says:

  Dear editor,
  The double standard of somali region specially the leadership, I am born grown in the said area, Somali and Oromo have never faced any boundary problem. The somali rgeion is the most in need of this ethnic federalism because it was not accessable and unknown. The term we often use for somali is Miigoo means very tiny and skeleton. I am surprised somali fighthing with Oromo on border dispute …the same issue was raised before 2005/6 the refredum in 420 kebeles 80% voted for Oromia. The feederalism clearly stuplated border dispute between the states (regions) that was done in refrundum held why now, is it a proxy war? Or Physological about wolqayit…I am honest!Somali-war on Oromo is like self burning for somali side. Politically speaking Oromos donot consider somalis like enemy everytime i talk with there one evil man behind the attack Abdi Omer (somali rgion presidant). Shame on you. the other surprise, the federal goverment slow reaction what if the attack happened another regions like x vs y. This is constituional issue who should protect the constituon? The difference between the talk and the reality? I am sure somali-Oromo brotherhood relation will shape to new dimensio

 5. Anuwar Bedhane says:

  the impartiality of this web is questionable, Dawit stand for ur mind one day the regime will pass but the people will live for ever, i was readining interesting comment by some body called M.Begna but you suddenly delete by quick i hope the comment fits to professional standard either close the site or entertain the feeling of all of us

 6. Nana says:

  ሁሉንም ነገር ወደ ፓለቲካ መቀየር የሚፈልጉ ጥገኛ ሠዎች አላማቸው ስልጣን ብቻ ነው ፡፡ የተፈጥሮም ሆነ ሠው ሠራሽ አደጋ ለነሡ ደስታ ነው ፡፡ወያኔ ነው ያደረገው ለማለት ይመቻቸዋላ ፡
  ለነገሩ መሀይማንን ማን ይቀየማል ፡፡

  ማነህ እዛጋ , ባለፈው ዝናብ ያስቀረው ወያኔ ነበር እንዳትለን ፡፡
  አንተኛው ,ሚስትህ ከሌላ የተኛችው ወያኔ አሳስቷት ነው ?
  ኦ ብራዘር ,ወያኔ ነው ፀጉርህን የመለጡው ፦ ሆድህንም ያንዘረጠጠው ????ቂቂቂቂቂ

 7. Nana says:

  ብልህ ግን ሁሌ ለሚጋጥመው ነገር ማንም ላይ ሣያላክክ ለለውጥ ይሠራል ፡፡
  መናን ሣይጠብቅ ወዙን አፍሶ ይኖራል ፡፡በሠውም በፈጣሪም ሣያሣብብ ችግሩን ለመፍታት ይጥራል ፡፡
  እንደባልቴት ተረትና ሀሜት አያበዛው ፡፡ ከሁሉ በላይ

  ‘ልቀቁኝ እሮጣለው !!!ዘራፍ ቁንጫ ገዳይ ፡፡’ አይልም !!!!

 8. Nana says:

  ድህነት አይኑ ይጥፋ እርግፍ ያርገው ጥርሡን
  ክቡሩን ወገኔን ምርጡን ኢትዮጵያዊ ማቅ ያለበሠውን ፡፡
  አትልቀቅ አካፋ አትጣል ዶማህን
  አታቁም ግንባታ ማወቅ መማርህን
  ያኔነው ድህነት ሚ’ያጠፋው ደብዛህን ፡፡
  ለወሬ ግዜ አትስጥ በሃሜት ለከበረ
  እሱ ነው ጠላትህ ከድህነት ያበረ
  ተጣላ ፦ ተቧጨቅ ምንትጠብቃለህ ብሎ እየፎከረ
  የድህነት ጠበቃ ወኔው የከዳው ሠው ቅስሙ የተሠበረ፡፡

 9. Papa Tango says:

  The 11% economy growth of tplf for the people of ethiopia is to eat from the garbage live in the garbage and buried in the garbage

 10. dergu temelese says:

  Ethiopia: The body count at a garbage dump tells another story (The Washington Post)

  Rescuers work at the scene of a garbage landslide, on the outskirts of the capital Addis Ababa, in Ethiopia on Sunday (AP Photo/Mulugeta Ayene)
  Ethiopia boasts about its economic progress. The body count at a garbage dump tells another story.

  By Paul Schemm March 15

  Three days of national mourning began Wednesday for the victims of a catastrophic landslide at the Ethiopian capital’s main garbage dump that left at least 113 bodies buried under a wall of trash and dirt, mostly women and children.

  This year has not been kind to Ethiopia, including widespread popular unrest, drought in many parts of the country, a cholera outbreak and stampede at a culture festival. Yet the deaths at the Addis Ababa landfill on Saturday stands out as a sobering counterpoint to the country’s boasts of economic progress.

  Ethiopia’s government for the last decade has tried to put behind the familiar cliches in Western minds of famine and poverty. The numbers help their case. Ethiopia has one of the best-performing economies in Africa. But 30 percent of Ethiopia’s population still lives below the poverty line.

  The changes are especially apparent in Addis Ababa, which was once little more than an overgrown village with a few government buildings. The city is now sprouting with glass and metal skyscrapers ringed by affluent new neighborhoods catering to an emerging middle class.

  But the landfill tragedy is a reminder that the slums and shantytowns are still there, too. One of them was built amid the artificial mountain of garbage, where people scrap out a living combing through the refuse. Late Saturday, they heard a roaring sound. The garbage mountain suddenly gave way, sweeping away makeshift homes and burying dozens.

  The growth of the capital has often outstripped efforts to manage it, creating hazards like the half-century-old landfill of Reppi, also known as Koshe or dirt in Ethiopia’s Amharic language.

  Located southwest of the city, just a 15-minute drive from the embassy-filled neighborhood of Old Airport that is also home to the city’s best international school, this mountain of trash is now surrounded by housing developments.

  Here, hundreds of men, women and children known as “scratchers” comb through the daily trash deliveries from the rest of the city, squabbling over the highly prized refuse from the wealthier neighborhoods that yield the most valuable castoffs or the best food. Overhead birds circle the more than 70-acre site, waiting for their own turn on this artificial mountain of trash.

  Even before the latest collapse claimed dozens of lives, injuries and deaths from the settling trash or the bulldozers were common in this area, which is often a first port of arrival for immigrants from the countryside.

  There was an attempt recently to close down the Koshe dump. But protesters from the surrounding Oromo region blocked garbage trucks heading for a new site.

  In sharply worded statement Monday, Amnesty International held the government responsible for this “totally preventable disaster,” saying that the government was aware it was at full capacity but used it anyway and allowed people to build their huts on the garbage.

  “These people, including many women and children, had no option but to live and work in such a hazardous environment because of the government’s failure to protect their right to adequate housing, and decent work.”

  An estimated 300 people scavenge through the rubbish mountain at any given time and it is feared that the death toll could keep rising. The tally of dead rose sharply Wednesday from 72 to at least 113, an Addis Ababa official, Dagmawit Moges, told the Associated Press.

  The government has announced the relocation of at least 300 people living on the site as well as compensation for the families. There have been scuffles though between residents and rescue workers, claiming they are not doing enough.

  In the days since the landslide, there has been a heavy security presence at the site.

  There has been no official reason for what caused the landslide, though the site’s overcapacity and the strain of accepting every day more garbage from the city’s estimated 3.5 million residents could be part of it.

  Some residents have also claimed that the trash mountain was destabilized by a small foreign-funded biogas facility on the site to harvest methane gas and part of a years-long (and so far unsuccessful) effort to eventually close down the landfill — an accusation denied by the government.

  Next to the festering, unstable landfill, that represents everything wrong with waste disposal across Africa and the developing world, is a project that could hopefully become a symbol of the continent’s future.

  The $120 million Reppie Waste-to-Energy facility is expected to be completed some time this year and would process 85 percent of the city’s trash, turning it into enough electricity to cover 30 percent of the household power needs of the city.

  The deal was announced in January 2013 with Cambridge Industries and construction started late in 2014. It is part of the country’s $150 billion Climate Resilient Green Economy project, with the stated of objective of turning Ethiopia into a middle-income economy by 2025 while keeping down greenhouse gas emissions.

  The plant will only process fresh garbage, so while it would not do anything about the mountain of refuse nearby, it would prevent future ones from being created — and possibly future tragedies from happening.

  The article has been updated to show that the size of the landfill is around 70 acres rather than 90 and the presence of a biogas project on the site that is distinct from the nearby waste-to-energy plant.

  Paul Schemm is the Post’s overnight foreign editor based in Addis Ababa, Ethiopia, joining the paper in 2016. He previously worked for the Associated Press as North Africa chief correspondent based in Morocco and prior to that in Cairo as part of the Middle East regional bureau.

 11. ethoash says:

  Thanks for the info ….. the news i remember not long time a go then the Sendafa oromo should be responsible… ETV should make interview how those Sendafa protester feel about it now ….can u imagine those Sendafa closed billion dollar investment… sendafa people opposed the billion dollar ቆሻሻ recycling facility saying it smell…

  here is my understanding to understand Ethiopian u have to understand jealousy

  it is very simple it is called jealousy… if u invest billion dollar then if we dont make money out of it then we wish u evil this is the same thing what happened in Tigray walkite TPLF invested billion dollar in sugar factory u would expected the normal people would be happy but not an Ethiopia they r so jealousy the protest the development because if they r not become rich no body will

  another logical understanding of the problem is kassa if u pay out 180,000 birr to farmer for his land the money might look big for the poor farmer but this farmer will finished the money with no time and he become homeless therefore paying money as kassa must be stopped instead land should be exchange for land if TPLF demolish house u should give them house not money

  if tplf take one hector of land u give them u give the farmer two hector of land or one hector of land and sweating the deal 180,ooo birr to go with it …. as i said the money should be deposed in bank and given to the farmer monthly and can be take out if the farmer want to buy technology

  my other point is garbage is a gold mine if u know what u r doing they can make u a lot of money u can start biogas business and sale the gas to the local for cooking if one house hole pay 100 birr per month and if u have 100.000 people then u r making ten million per month and 120 million per years for free garbage this doesnt count for plastic garbage that u r going to process and paper product and so on

  this is part one thought i will come back with my second thought by for now
  Top

  PART II

  harvesting methane gas is very easy all u need is tire inner tube and plastic dome over the garbage when enough methane gas collected u connect it to tire inner tube and the gas fill the inner tube and u have a cooking gas to sale … very easy technology to set up see this video

  now for safety reason u can keep the inner tube inside the tire with rim so that it is protected
  https://youtu.be/DXKe4zTjSJM

  another point is to make this economy going the government must give licence or permit for limited number of garbage collector for example if there r 100 or 1000 garbage collector making a living in that garbage landfill u give them a licence u fences the area and u tell them now u own this garbage landfill…. this alone will generate 100 million birr capital just by giving them licence and u will make those garbage collector very rich … now if the government make it the garbage collection and sorting benefit then those garbage collector will be more then happy to pay tax to government to keep their monopoly

  now when i come back to those farmers who lost their land …. they should be given kassa the question is what kind of kassa… the government must be smart if the market value of the land is 100,000 the government should offer them ten time of the market value so to make it the farmer to hit the jackpot …when ever the government land appropriation announce the land owner should jump in enjoy knowing the going to get ten time the value of their market price

  now u might ask how on earth the govt. will get ten time the price of the market value… simple

  let take the farmer in Sendafa

  let say the farmer in Sendafa have one hector of land and it the land valued at 180,000 birr

  now the government will this farmer two hector of land somewhere else and 180,000 birr

  now u think 180,000 birr is not ten time of the value of the land wait the bank will give them ten time loan that means the farmer will get low for 1.8 million birr against his 180,000 birr

  this is not done

  let say we will have 100 farmers who are getting kassa that means

  as the report 25 million birr or 40 million birr now u can give this money to the farmer and done with it or u can create one big share company and borrowed against this money which is ten time of 25 million birr which is 250 million birr granted by government

  now those 100 farmer have 250million birr from the bank

  if the government is smart they will not give them land instead of land they will start Ago industry that need 10 hector of land for all 100 farmers instead of 100 hector of land

  we can start hen production, milk production or one mega firm using modern technology this way we will save a lot of land from give in out to the farmer and still allowed them to make 60,000 birr per year from their new ago industries

  now some of them might want still want to farm but they dont want to move away from their home simple again u build them 1 million birr house in Sendafa and ask them to pay mortgage from their 60,000 birr income that the government give them per year this way the government will recycle the money back to the government bank when the farmer pay his mortgage

  you might ask how the government make money if they did not move the farmer and the farmer did not farm how the govt. got the money to pay the firm easy… virtual land ownership

  how this virtual land ownership work let say the farmer in Sendafa own land in Sendafa but the govt. took the land from him…. so what we do is we create government land bank

  let say the government own land in Gamballa and Arab investors come to invest and they need land the government can just give them land they have to take it from land bank so when one hector of land rent to the Arab investor the lease money goes to the Sendafa farmer not to government

  this means any Ethiopia can own land any where in Ethiopia as long as his virtual land ownership deposed in govt. land bank … so the farmer doesn’t have to go any where all he has to do is deposit the land in land bank and earn interest

  NIMBY stands for “not in my backyard” and refers to the situation that almost no community is happy to have a waste management (or any other similar) infrastructure erected on their territory,

  once i meet this white guy from small city and i ask him what is his town mean income u told me with his face beaming with pride we have the country jail….that is what he told me he is so proud to have jail in his town that provided job for many of them…you see Western countries know any infrastructure is good news for their tow unlike idiot empire in Ethiopia they opposed infrastructure … u implying those oromo people will not protest if they got sugar factor think Again in Tigray the Amhara district protest and willing to kill because TPLF build one billion dollar sugar factory how more sweet can u get then sugar … the Ambo oromo burn their own university… some time it make me laugh….

  one thing u said make point is the western govt. the community happy by building other infrastructure … that is very goooooooooooooood point

  to do this we have to value everything the Sendafa governor or city mayor must get million for allowing the landfill this way u make it a business deal … if the community know money coming to them they would have been fighting all over them to attract the next landfill so their community get need money to build all kind of the infrastructure they need

  i will go one more farther we should also start pay the community where we produce hydro for example we building Nile hydro but do those community going to get money from their resource or we will take billion out of their community without giving back this is what bread revolution and poverty …every city should get paid for their resource four stop

  now how the govt. get money to pay Sendafa governor or city mayor very simple the Addis Ababa residence must pay for their own garbage they cant just dump their garbage in Sendafa and make the Sendafa smell their garbage without paying for it ….this culture must be cultivated and adopted nothing is for free

  one more note the Sendafa garbage landfill can reduce the smell by harvesting the methane gas and use it for cooking and make money out of it and reduce the smell almost to zero

  i know it is long article but i am hopping Ethiopians who worry about this event will read it and understand how garbage landfill work…

  to those who live by the Garbage fill and who are affected by landslide should ride this sympathy wave … and ask the govt. to build them appropriate housing and create job for them instead of becoming the opp. tools they should use this event to improve their life and stand with the govt. and demand the govt. build them an appropriate housing just like they building condominium

  my dream is to build low cost housing for the pooooooooooooooooooooooooooor and make billion of dollar doing it

 12. dergu temelese says:

  ዳውን ዳውን ወያኔ !!
  መስፍን ማሞ ተሰማ
  ከወልቃይት ኮንሶ ምነው አይታረስ
  ከጋምቤላ ሐረር ምነው አይታረስ
  በኦጋዴን ምድር ምነው አይታረስ
  ሖራ ቢሾፍቱ ላይ ምነው አይታረስ
  በሬሳ ላይ አለፍን ካምና እስከዚህ ድረስ።
  ከተከዜ ወዲህ ልቅሶ በረከተ
  የትግራይን እንጃ ጦቢያ ግን አለቀ።
  ከተከዜ ወዲህ ሳቅ ተሰየፈ
  ከተከዜ ወዲህ ደስታ ተሰየፈ
  ከተከዜ ወዲህ ሠርግ ተሰየፈ
  ከተከዜ ወዲህ በዓል ተሰየፈ
  ከተከዜ ወዲህ ትምህርት ተሰየፈ
  ከተከዜ ወዲህ መኖር ተሰየፈ።
  ከተከዜ ወዲህ ህወሃት ጠነዛ ፤ ህወሃት ቆነሰ
  “ኢህአዴግ” ሻገተ ፤ ህወሃት ሸተተ።
  ጋላቢው ህወሃት – ብአዴን ኦህዴድን አሞሌ እያላሰ
  ደህዴግ ፈረሱ ሀይሌ አስመለሰ
  አየር ተበከለ ፤ ጤና ተቃወሰ ፤ ሠላም ደፈረሰ።
  የመለስ ነፍስ አባት ሲኞር ገብረመድህን (የሁዋለኛው ጳውሎስ)
  ጢሙን እየላገ እጅግ ተደነቀ ፤ እጅግ ተገረመ
  ለካስ “ወንጌላዊው” ፤ ለካስ ሀይለማርያም ከርሱም የረቀቀ ሳጥናኤል ነበረ።
  የጣሊያኑ ውላጅ የሙሶሎኒ ልጅ መለስ ተበሳጨ፤ በቅናት አረረ
  እርሱ የፈጠረው “ወንጌላዊው” ሀይሌ ከርሱም ስለናረ ፤ ከርሱም ስለላቀ።

 13. ዜጎችን በጅምላ ማሰር ማሰቃየት እና ማስራብ ወደ የእርስበርስ ዕልቂት says:

  ዜጎችን በጅምላ ማሰር ማሰቃየት እና ማስራብ ወደ የእርስበርስ ዕልቂት .
  https : // www. youtube .com/watch?v=qxaUBqJNaVI

  በህወሃት የታፈነው ድርቅ ወደ ረሃብ እያደገ ነው፤ ት/ቤቶች ተዘግተዋል!

  March 25, 2017 .
   የኢትዮጵያ ሶማሌ ዘጠኙም ዞኖች ሙሉ በሙሉ የድርቁ ሰለባ ሆነዋል! March 25, 2017
   በክልሉ 437 የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከድርቁ ጋር በተያያዘ ተዘግተዋል፤ March 25, 2017
   183,090 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል!
   ዜጎችን በጅምላ ማሰር ማሰቃየት እና ማስራብ!
   የእርስበርስ ዕልቂት ያሰጋል! March 25, 2017
  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሁለት ወራት ውስጥ ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች ምስራቅ አፍሪካ የከፋ ድርቅ መከሰቱንና ዓለም የዕርዳታ እጆቹን ለአገራቱ እንዲዘረጋ በተከታታይ ሪፖርቶቹ ተማጽኗል፡፡ እንደ በዘገባው ከሆነ ድርቁ የከፋባቸው ተጠቃሽ አገራት ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡
  ከኢትዮጵያ ውጭ የተጠቀሱት መንግሥታት ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የዕርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት፤ በተባበሩት መንግሥታት በኩል የአውሮጳ ህብረትና ሌሎች ለጋሾች በከፋ ድርቅ ላይ ለሚገኙት አገራት ዕርዳታ እየሰጡ ናቸው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ሪፖርት መሰረት አገራቱ በእርስበርስ ጦርነት የሚታመሱ እና በውስጥ ችግራቸው የፖለቲካ አለመረጋጋት የሚታይባቸው የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች የነገሰባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም ድርቁ ዜጎቻቸውን ለስደት ከመዳረግ አልፎ አገራቱን ለከፋ ማህበራዊ ቀውስና ለውስጥ አለመረጋጋት እየዳረጋቸው እንደሆነ ሪዘገባው ያመለክታል፡፡
  “(ረሃቡ) በራስ አቅም የሚፈታ ችግር ነው” ህወሃት
  ከዜጎች ችግር በላይ ለአገር ገጽታ ግንባታ የሚጨነቀው ህወሃት/ኢህአዴግ ኃላፊነት በሚሰማዉ መልኩ ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመንቀሳቀስ ድርቅ በተከሰተባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ተገቢ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ችግሩን “በራስ አቅም የሚፈታ ችግር ነው” በሚል ባሳየው ዳተኝነት ድርቁ ወደ ረሀብ እንዲያድግ ከማድረግ ውጪ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሲሰጥ አልታየም፡፡
  ከህወሃት/ኢህአዴግ ፍላጎት ውጪ ቢሆንም አዲሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፤ ኢትዮጵያ የተረጋገጠባትን ድርቅ እንድትቋቋም ዓለአቀፉ ማኅበረሰብ በጋራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ ያም ሆኖ ዕርዳታው በሚፈለገው መጠን ሊገኝ አልቻለም፡፡ ለዜጎች ስቃይ ደንታ ቢስ የሆነው የህወሃት አገዛዝ በዓለምአቀፍ መድረኮች የእርዳታ ጥሪ ከማቅረብ ይልቅ፤ የአገሪቱ “አዳኝ መሲህነቱን” መስበኩን ተያይዞታል፡፡ ውጤቱም የዜጎችን ነገ በማጨለም የረሀብ ቤተሰብ የሆነ ተስፋ የለሽ ትውልድ ማፍራት ሆኗል፡፡
  “ልማት የረሃብ አደጋን ያጠፋል” (መለስ፣ 1887)፣
  “ራሱን የቻለ በራሱ የሚቆም ከልማት ጋር ያልተቆራኝ የረሀብ ማጥፋት ፖሊሲ ያስፈልገናል” (መለስ፣ 1992)፣
  “ዕድገታችን የረሀብ አደጋን ቀንሶልናል” (መለስ፣ 2004)፣
  “ማንኛውንም ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችል አቅም መገንባት ችለናል” (ኃይለማርያም፣2008)፣ …
  እየተባለ በህወሃት/ኢህአዴግ ሲስተጋባ የኖረው ፕሮፓጋንዳ በእዉን የማይጨበጥና የማይዳሰስ መሆኑን እየታዘብን ነዉ፡፡ በአገሪቱ “አለ” የተባለዉ “ዕድገት”ም በምግብ እህል ራስን ለማስቻልም ሆነ ከዉጭ እርዳታና ድጎማ ለማላቀቅ የቻለ አይደለም፡፡ የመንገድ እና የፎቅ ግንባታውም የድሃውን ጉሮሮ የሚዘጋ የዕለት ጉርስ ወደመሆን ሲቀየርና ህይወቱ ሲያሻሽል አልታየም፡፡ የተለመደው የድርብ አኻዝ “ዕድገት” ግን አሁንም ይደሰኮራል፡፡
  በቀደሙት ሁለት ተከታታይ ዓመታት የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተከሰተዉን ድርቅ ለመቋቋም 16.5 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን “የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን” በህዳር/2009 ዓ.ም. ይፋ ያደረገዉ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በ2007/2008 ዓም አስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው የነበሩ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር 11.2 ሚሊዮን እንደነበረ የሚገልጸው ሪፖርት በ2009 ዓ.ም ወደ 5.6 ሚሊዮን ዝቅ እንዳለ ይናገራል፡፡
  ሁሌም ቢሆን ከአህዛዊ መረጃዎች ጋር የተአማኒነት ችግር ያለበት ህወሃት/ኢህአዴግ አሁንም ቢሆን በፖሊሲ መክሸፍ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት፣ በሙስናና በብልሹ አሰራሮች ምክንያት እየተባባሰ ያለውን ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ጋር (ብቻ) ማያያዝን መርጧል፡፡ በድርቁ የተጠቁ ዜጎችን ቁጥርም በተመሳሳይ መልኩ አዛብቶ በማቅረብ ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት ጥረት ሲያደርግ ይስተዋላል፡፡ በአገሪቱ ታሪክ ድርቅ አጥቅቶት የማያውቀው የደቡብ ኢትዮጵያ ቆላማ ክፍል በዘንድሮ ዓመት ድርቁ ከጎበኛቸው ክልሎች አንዱ ሆኖ ባለበት ሁኔታ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት አጥጋቢ ዝናብ እንዳልታየ እየታወቀ፤ አገሪቱ ሠላምና መረጋጋት ርቋት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች መዳከማቸው እየታየ “አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልግቸው ዜጎች ቁጥር በእጥፍ በመቀነስ ወደ 5.6 ሚሊዮን ወርዷል” በሚል የድርቁን አስከፊ ገጽታ ለማፈን ህወሃት ጥረት ላይ ይገኛል፡፡
  በ2007-2008 ዓም የተረጂዎች ቁጥር 11.2 ሚሊዮን ደርሶ እንደነበር በህወሃት/ኢህአዴግ ቀጥተኛ ትዕዛዝና ቁጥጥር ሥር ባሉ የሚዲያ ምንጮች ይፋ እንደሆነ የሚታወስ ነው፡፡ ከምርጫ 2007 በኋላ ኢትዮጵያ የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ እንደገባች ይታወቃል፡፡ የህዝባዊ አመፆች ውጤት በሆነዉ የፖለቲካ አጣብቂኝ፣ የኢኮኖሚ መዳከምና የማህበራዊ እንቅስቃሴዎች መዛል ሁለንተናዊ ችግር ውስጥ ባለቸው ኢትዮጵያ፤ የዕለት ምግብ ደራሽ ተረጅ ዜጎች ቁጥር በምን ተዓምር በእጥፍ ቀንሶ 5.6 ሚሊዮን ብቻ ሊሆን ቻለ? መልሱ ቀላል ይመስላል፡፡ የዕለት ምግብ ደራሽ ተረጂ ዜጎች ቁጥር የቀነሰው ወረቀት ላይ በሚቀርቡ ሪፖርቶች እንጂ መሬት ላይ ባለው እውነታ አይደለም፡፡
  ከአገሪቱ ውስጣዊ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በተለየ መልኩ ያለፉት ሁለት ዓመታት እንኳንስ ተደጋጋሚ ድርቅ ለሚጎበኛቸው የኢትዮጵያ ክልሎች፤ ለመሀል አገር ከተሞችም የኑሮ ውድነቱ ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ አደባባይ ላይ የተሰጣ እውነት ነው፡፡ “የአፍሪቃ መዲና – የኢትዮጵያ ህዳሴ ተምሳሌት” በሚባልላት አዲስ አበባ በድሆች በመከበቧ ሥራ ለምግብ፤ የሆነው የሴፍቲኔት ፕሮግራም እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡ ችጋሩ በዚህን ያህል መጠን አፍጦ ባለበት ወቅት ከቁጥር ጋር ድብብቆች የያዙት የህወሃት/ኢህአዴግ አመራሮች የክህደት መስመራቸውን ማጠናከሩን ተያይዘዉታል፡፡
  “የአስራ አንድ በመቶ ዕድገት አስመዝግቤአለሁ” የሚለው ፕሮፖጋንዳና ተደጋጋሚ የድርቅ ዜና ዘገባዎች ያልተጣጣሙለት ህወሃት/ኢህአዴግ ማጣፊያው ቸግሮት “ድርቁን በራስ አቅም/ጥረት እንቋቋማለን” ሲል ቢቆይም፤ የድርቁን ተስፋፊነት ከመጨመር ባለፈ እንደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ባሉ ቦታዎች ድርቁ ወደ ረሃብ ደረጃ እንደደረሰ ጎልጉል ከክልሉ ያጠናቀረው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሆኖም ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር እያለ የሚጠራው ህወሃት አሁንም “(ረሃቡ) በራስ አቅም የሚፈታ ችግር ነው” በሚለው ፕሮፓጋንዳው ገፍቶበታል፡፡
  የኢትዮጵያ ሶማሌ ከድርቅ ወደ ረሀብ!
  የኢትዮጵያ ሶማሌ በታወቀ ምክንያት ልዩ የሆነ የፖለቲካ ትኩረት የሚሻ ክልል ነው፡፡ ፖለቲካዊ ትኩረቱ የክልሉን ተወላጆች ወደ ማዕከላዊ መንግስት የሥልጣን ቦታ ከመሳብ ጀምሮ የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ከመሀል አገር እንቅስቃሴዎች ጋር እየተመጋገቡ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲያሳዩ በሚያስችል መልኩ ልዩ ድጋፍ ሊደረግለት የሚገባ ክልል ነበር፡፡

  190 በጎችና ፍየሎች እንዲሁም 23 ከብቶች የሞቱባቸው ወ/ሮ ፋጡማ – አሁን ከ190ው 10፤ ከ23ቱ 2 ቀርቷቸዋል (ፎቶ: አቢይ ጌታሁን Oxfam)
  እውነታው ግን ከዚህ በተቃራኒው የኢትዮጵያ ሶማሌ ከኢትዮጵያ የተነጠለ ግዛት እስኪመስል ድረስ፤ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ለማዕከላዊ መንግስቱ ባይተዋር፣ ከኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው የተገፉ፣ በማህበራዊ መስተጋብሩ የሌሉበት፤ ዝግ ክልል ሆኗል፡፡ በዚህ የተነሳ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተወላጆች ኢትዮጵያን ያለ ፓስፖርት የሚንቀሳቀሱባት ጐረቤት አገር እንጂ አንደ አገራቸው ሲመለከቷት አይስተዋልም፡፡ ምንግዜም ቢሆን የመገፋት ውጤቱ ይኸው ነው፡፡
  የገዢው ፓርቲ አጋር ድርጅት በሆነው ሶህዴፓ (የሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) የሚመራው ይኸው ክልል፤ በብዙ መንገድ ከመረጃ የተነጠለና የተዘነጋ ክልል ነው፡፡ በተለይም ኦጋዴንና አካባቢው ፍፁም የተረሳ ሆኗል፡፡ በተደጋጋሚ የድርቅ ሰለባ ከሚሆኑት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ሶማሌ ከ2007 ዓም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ከባድ ድርቅ በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም የሶማሌን ድንበር ተጠግተው ያሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ (ኦጋዴን) አካባቢዎች በድርቁ ሙሉ በሙሉ ተጠቂ እንደሆኑ በክልሉ ከሚንቀሳቀስ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጎልጉል ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡ “ሕይወት በኢትዮጵያ ሶማሌ እየቆመች ነው” የሚሉን የመረጃ ምንጮቻችን በክልሉ ካሉ 9 ዞኖች ውስጥ ሁሉም ዞኖች በድርቁ ክፉኛ እንደተጠቁ ይጠቁማል፡፡ “በተለይም በኦጋዴን፣ ሸበሌ፣ ቀብሪደሃር፣ ቆራሄና ደጋሃቡር ላይ ኮሌራን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች የተከሰቱ በመሆኑ የድርቁን ማህበራዊ ቀውስ ከቀን ወደ ቀን አብሰውታል” የሚሉት የአካባቢው ምንጮች ከዕርዳታው ማነስ አኳያ በእነዚህ አካባቢዎች ድርቁ ወደ ረሃብ ማደጉን ይናገራሉ፡፡
  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል፤ ኦጋዴንና አካባቢው በህወሃት/ኢህአዴግ እና ክልሉን በሚመራው ሶህዴፓ የተገፋና ሆን ተብሎ የተነጠለ፣ የሰብዓዊ መብት ረገጣው የከፋበት፣ ለዓመታት በቀየው የርስ በርስ ጦርነት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው የደቀቀ በመሆኑ፤ ወትሮውንም የአካባቢው ነዋሪዎች ከዕለት ተረጅነት የተላቀቁ አልነበሩም፡፡ ሞት ወይም አካባቢውን ለቆ መሰደድ ዕጣ ፈንታቸው የሆነው የኦጋዴን ነዋሪዎች ለሦስት ተከታታይ ዓመታት (2007 – 2009 ዓም) በክልሉ የደረሰው ድርቅ የከፋ በመሆኑ ከቀደመው ዓመታት የባሰ የችጋር ዘመን በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ አልፎም የኦጋዴን ህዝብ በህወሃት የዘር ማጥፋት የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ ሆኗል፡፡
  ዛሬ ላይ የሶማሌ ክልል ድርቅ በኦጋዴን ብቻ የተገደበ ሳይሆን ዘጠኙንም የክልሉን ዞኖች ያዳረሰ ሆኗል፡፡ እንደ ጎልጉል የመረጃ ምንጮች በሶማሌ ክልል ያለው ድርቅ መጠን ሰፊ ሲሆን፤ የክልሉን ዋና ከተማ ጅግጅጋን ጨምሮ በዞን ከተሞች የሚኖሩ ህፃናት ከሚጠበቅባቸው ክብደት በታች ያሉ፤ የንፁህ መጠጥ ውሃ እጦት ያለባቸው፤ ከሌሎች ሸቀጦችና ግልጋሎቶች አንፃር የምግብ ዋጋ ግነት የሚታይባቸው መሆናቸውን ይጠቁማሉ፡፡ እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክ መስሪያ ቤት የሶማሌ ክልል የህዝብ አሰፋፈር ሪፖርት፤ በክልሉ በከተማ የሚኖረው የህዝብ ብዛት 18.2% ሲሆን፤ በገጠር የሚኖረው ደግሞ ከአጠቃላይ የክልሉ ህዝብ አኳያ 81.8% ያህል ነው፡፡ ከዚህ አሃዛዊ መረጃ ተነስተን፤ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ከመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ ከመልከዓ ምድራዊ አለመመቸት፣ ከተበታተነው የክልሉ ህዝብ አኗኗር እና ከዕርዳታ መጠን ማነስ አኳያ ወደ ገጠሩ አካባቢ የዕርዳታ ተደራሽነቱ እየሳሳ የሚሄድ በመሆኑ የድርቁ አስከፊነት ከፍ ያለ እንዲሆን አድርጐታል፡፡ ወደ ረሃብ ለማደጉ ዋነኛ መንስኤ እነዚህ ተግዳሮቶች ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡
  በተለይም ደገሃቡር (5 ወረዳዎች ያሉት)፣ ቆሬህ (4 ወረዳዎች ያሉት)፣ ጎዴ (7 ወረዳዎች ያሉት)፣ አፍዴር (9 ወረዳዎች ያሉት) እና የኦጋዴን አካል የሆኑ የክልሉ 4 ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 25 ወረዳዎች ድርቁ እየከፋ በመምጣቱ ወደ ረሃብ በማደግ ላይ እንደሚገኝ በክልሉ ከተሰማሩ የግብረሰናይ ድርጅት ባልደረቦች ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ይጠቁማሉ፡፡
  ባሳለፍነው ሳምንት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ ከድርቁ ጋር ተያይዞ ኦጋዴን ውስጥ በተቀሰቀሰ የኮሌራ ወረርሽኝ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ሁለት ሺህ ዜጐች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ከዚህም ሌላ በቂ የህክምና ድጋፍና የመድሃኒት አቅርቦት እንደሌለ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡
  ጎልጉል የአካባቢውን የመረጃ ምንጮች በመጠቀም ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ጥረት፤ በኦጋዴን አካባቢ የኮሌራና የተቅማጥ በሽታ የተከሰተ መሆኑንና በዩኒሴፍ ስር ያሉ የህክምና ባለሙያዎች በማዕከል (በዞን) እና በንዑስ ጣቢያዎች ደረጃ የህክምና ዕርዳታ እየሰጡ ቢሆንም፤ በገጠር ነዋሪ የሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ አለመኖሩን አረጋግጧል፡፡ እንደ ተቅማጥ ያሉ ተላላፊና ሌሎች ውሃ ወለድ በሽታዎች በዋርዴር፣ ፊቂ፣ ሊበንና ሽንሌ ዞኖች ውስጥ ባሉ 22 ወረዳዎች እንደሚታይ የጎልጉል የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡
  በክልሉ ውስጥ ሰብዓዊ ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የእርዳታና የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት (UNOCHA) ከአንድ ወር በፊት “Ethiopia; Activities and Resource Gap for closed Schools in Drought Affected Areas of Oromia and Somali Regions” (በኢትዮጵያ በድርቅ በተጠቁ የኦሮሚያና የሶማሊ ክልሎች በተዘጉ ት/ቤቶች ያለው የእንቅስቃሴና የሃብት ክፍተት) በሚል ባወጣው ሪፖርት በክልሉ ውስጥ 437 የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከድርቁ ጋር በተያያዘ ተዘግተዋል፡፡ 183,090 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል፡፡ ምግብና ውሃ ፍለጋ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ አባወራዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ይኽው ሪፖርት ይጠቁማል፡፡ እጅግ አሳዛኙ ነገር በምግብና ውሃ ፍለጋ ምክንያት ከተፈናቀሉት አባወራዎች ጋር 180,600 የሚሆኑ ታዳጊ ህፃናት እድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ መሆኑ ነው፡፡ ይህንን ቁጥር ከድርቁ ጋር በተያያዘ ትምህርታቸውን ካቋረጡ ተማሪዎች ጋር ስንደምረው የክልሉን የትምህርት ሽፋን አንሸራቶ ቁልቁል የሚቀብረው ይሆናል፡፡ የአካባቢውን ሕዝብ ኑሮ ሊቀይር የሚችለው የነገው ተስፋ አሁን ባለበት ድህነት ላይ ድንቁርና ተደግሶለታል፡፡
  በክልሉ ውስጥ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ከተዘጉት 437 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አርባ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፡፡ በእነዚህ ት/ቤቶች ይማሩ ከነበሩ ተማሪዎች በ2009 የትምህርት ዘመን የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ (የ10ኛ ክፍል ማትሪክ) ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም፡፡ በአገርአቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና መርሃ ግብር መሰረት የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (የ10ኛ ክፍል ማትሪክ) እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (የ12ኛ ክፍል ማትሪክ) ከአንድ ወር በኋላ በግንቦት ሁለተኛና ሦስተኛ ሳምንት በተከታታይ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በረሃብ አንጀታቸው የታጠፈ የሶማሌ ክልል ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከማቋረጣቸው ጋር ተያይዞ የማትሪክ ፈተና ላይ በምን አግባብ ሊቀመጡ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠው አቅጣጫ የለም፡፡
  የሶማሌ ክልል ድርቅ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት የቀጠለ ቢሆንም እንደ ዘንድሮው ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ትምህርት ቤቶች ከድርቅ ጋር ተያይዞ ተዘግተው እንደማያውቁ የሚገልፁት የአካባቢው የጎልጉል ምንጮች፤ ቀድሞውንም በዘርፈ ብዙ ችግሮች ተተብትቦ የነበረው የክልሉ የትምህርት ጥራት ጉዳይ አስታዋሽ አልባ ሆኗል፡፡ አርብቶአደር የሆነው አብዛኛው የክልሉ ነዋሪ ለእንስሳቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከቦታ ቦታ በተንቀሳቀሰ ቁጥር አብረዋቸው የሚንቀሳቀሱ ትምህርት ቤቶች /Satellite Schools/ በዩኒሴፍና በዩ.ኤስ.ኤድ ድጋፍ ሰጪነት ተቋቁመው የነበረ ቢሆንም ከድርቁ ጋር በተያያዘ እነዚህ ተንቀሳቃሽ ት/ቤቶች እና ከፊል መደበኛ ት/ቤቶች ሊከስሙ ችለዋል፡፡
  ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ድርቁን ለመከላከል ሲደረግ የነበረው ጥረት፤ የክልሉን ነዋሪዎች ከመርዳት ጐን ለጐን ለእንስሳትም የሚሆን መኖ ከማዕከል እየቀረበ የእንስሳቱን ሕይወት ለማቆየት ጥረት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም በዘንድሮ ዓመት የእንሰሳት መኖ ቸል የተባለ ጉዳይ በመሆኑ፤ ከዚህም ባለፈ በበልግ ወራት የሚጠበቀው ዝናብ ከነጭራሹ በመቅረቱ የአርብቶ አደሮች እንሰሳት ቁጥር በመመናመን ላይ ይገኛል፡፡ ለእርዳታ ምቹነት በሚል በየአካባቢው ተበታትኖ የሚኖረውን አርብቶአደር በየማዕከሉ ለመሰብሰብ በሚደረገው ጥረት እንሰሳቱ ከግጦሽ ቦታቸዉና ከወራጅ ወንዞች እየራቁ እንዲሄዱ ያደረጋቸው በመሆኑ ከመኖ እጥረቱ ጋር በተያያዘ የእንሰሳት እልቂት የሚጠበቅ ነው፡፡ እንሰሳቶቻቸውን ባጡ ቁጥር ከህይወት ሰልፍ እንደወጡ የሚቆጠሩት የክልሉ አርብቶአደሮች ቀጣይ ህልውና ምን ሊሆን እንደሚችል አሳሳቢ አድርጎታል፡፡
  በእርዳታ አሰጣጥ ደንብ በየቀኑ በነፍስ ወከፍ ለአንድ ሰው 5 ሊትር ውሃ መቅረብ እንዳለበት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊና የእርዳታ ድጋፍ ድርጅት (UNOCHA) መመሪያ ይደነግጋል፡፡ ይሁንና በክልሉ ካለው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ውስንነት የተነሳ በአማካይ በነፍስ ወከፍ 2.1 ሊትር ውሃ በየቀኑ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሚጠቁሙት የጎልጉል የመረጃ ምንጮች የውሃ አቅርቦቱ እንደ እርዳታ ማስተባበሪያ ማዕከሎች ቅርበትና ርቀት የሚወሰን መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በዚህም የተነሳ በአማካይ 2.1 ሊትር ዉሃ በተሟላ መልኩ የማይዳረስባቸዉ ቦታዎች እንዳሉ ይገልጻሉ፡፡

  .
  በክልሉ 18 የማገገሚያ ጣቢያዎች ተቋቁመው የምግብ እጥረት የገጠማቸዉና ከክብደት በታች ላሉ ህጻናትና ለነፍሰ ጡር/የሚያጠቡ እናቶች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም፤ ከተረጂዎች ቁጥር አኳያ የማገገሚያ ጣቢያዎች በቂ እንዳልሆኑ በህክምና ሙያ የተሰማሩ የጎልጉል የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ ተንቀሳቃሽ የህክምና ቡድኖች ቢኖሩም በገጠሩ ክፍል ተዘዋውሮ የህክምና እርዳታ ለማደረግ የሚያስችል የመሰረት ልማት አቅርቦት ባለመኖሩና በክልሉ ገጠራማ ቦታዎች በተለይም በኦሮሚያ አዋሳኝ ቦታዎች የደህንነት ስጋቶች የሚታይ በመሆኑ ህክምናው በዋናነት በማዕከላት እና በንዑስ ጣቢያዎች የተገደበ ሆኗል፡፡ በዚህ የተነሳ በገጠሩ ክፍል ተቅማጥና ኮሌራ የመሳሰሉት ተላላፊ በሸታዎች ሊከሰቱ ችለዋል፡፡
  ለእያንዳንዱ ሰው በነፍስ ወከፍ በወር 15 ኪሎ ግራም ስንዴ፣ በቆሎ (እህል)፣ ዘይት፣ አልሚ ምግብ ማደል የሚገባ ቢሆንም፤ እርዳታው ወጥነት ባለው መልኩ ሊደርስ አልቻለም የሚሉት የአካባቢው መረጃ አቀባዮች፤ ከዞን ከተማዎች ራቅ ባሉ ቦታዎች የሚገኙ የእርዳታ ማዕከላት እስከ ሁለት ወር ድረስ እንደሚዘገይ ይናገራሉ፡፡ ክልሉ ከማዕከላዊ መንግስቱ ራቅ ያለ መሆኑና ለሚዲያ ዝግ የሆነ ባህርይ የሚያሳይ በመሆኑ የክልሉ ድርቅ እንደታፈነ የሚያምኑ አስተያየት ሰጪዎች፤ የዚህ ሁሉ ሥረ-ምክንያት የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ውጤታማ አለመሆን የወለዳቸው ችግሮች እንደሆኑ ያምናሉ፡፡
  ከድርቅ ወደ ረሃብ … ከረሃብ ወደ እርስ በእርስ እልቂት?!
  በኢትዮጵያ ሶማሌ የተከሰተው ድርቅ ለተከታታይ ዓመታት ቀጣይነት አሳይቷል፡፡ የበልግ ወራት ዝናብ አለመገኘቱ፤ የውሃ እጥረት መኖሩ፤ የክልሉ መልከዓ ምድርና የህዝቡ አሰፋፈር ለእርዳታ አሰጣጥ የማይመች መሆኑ (የመሰረተ ልማቶች አለመሟላት)፤ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በበቂ ሁኔታ ለእርዳታ እጁን መዘርጋት አለመቻሉ ረሃቡን አስከፊ እያደረገው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በተከታታይ በታዩ ህዝባዊ አመፆች በመደናገጡና የገባበት ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ድርቁን ቸል እንዲለው በማድረጉ፤ በክልሉ ውስጥ ካለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች ጋር ተያይዞ የዕለት ምግብ ደራሽ ተረጂዎች ቁጥር ሊጨምረው እንደቻለ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፤ በቀጣይ ለድርቁ ዘላቂ መፍትሄ እስካልተቀየሰ ድረስ የክልሉ ነዋሪዎች በረሃብ መርገፋቸው አይቀሬ መሆኑን ይጠቁማል፡፡
  ህወሃት/ኢህአዴግ በተደጋጋሚ እየፈፀመ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና አፈና የለጋሽ አገራትን እጅ እያሳጠረው መጥቷል፡፡ “እርዳታው ነፃ ማህበረሰብ እንዳይፈጥር ለማፈን ይጠቀምበታል” እየተባለ በለጋሽ አገራት የሚብጠለጠለው ገዢው ኃይል ለዜጎች ስቃይ ደንታ ቢስ መሆኑን ቀጥሎበታል፡፡ ከመሬት ፖሊሲው ርዕዮተዓለማዊ ስህተት የሚነሳው ህወሃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ፖሊሲ ክሽፈቶች፤ በተዘጋ የፖለቲካ ሥርዓት እና ገበሬዎችን የራሱ ጭሰኛ ባደረገ ቀፍዳጅ ፖሊሲው በመቀጠሉ በቀላሉ በአገራዊ የምርት ክምችት መመከት የሚቻለው ድርቅ ወደ ረሃብ እያደገ ሲሄድ እየታየ ነዉ፡፡ ድርቁ ወደ ረሃብ ከማደጉ ባሻገር ረሃቡ ከውስን የተፈጥሮ ሃብት ቅርምት ጋር ተያይዞ ድንበር ተዋሳኝ ክልሎችን ወደ እርስ በርስ እልቂት መግፋቱ ተጠባቂ ስጋት ሆኗል፡፡
  በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ህልፈት መንስኤ የሆነው፤ ከ35 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የተፈናቀሉበት፤ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል መሀከል የተፈጠረው የድንበር ግጭት ዋና ሥረ-ምክንያት በሁለቱም ክልል የተከሰተው ድርቅ ወደ ረሃብ በማደጉ ነው፡፡ ድርቁ ወደ ረሃብ በማደጉ በክልሎቹ ድንበር ያለዉን ውስን የተፈጥሮ ሀብት (የግጦሽ ቦታ፣ ወራጅ ወንዞችና አንጻራዊ ለም መሬት) ለብቻ ለመቀራመት በተፈጠረው ግብግብ ቀላል የማይባል ሰብዓዊ ጥፋት ደርሷል፡፡ ለጊዜው የራበው ህዝብ መሪውን ሲበላ ባይታይም እርስ በርሱ ሲተላለቅ ግን ተስተውሏል፡፡
  ጥቂት የሥርዓቱ ተጠቃሚዎችን የበለጠ በሃብት እያገዘፈ ብዙሃኑን ወደ ድህነትና የኑሮ ቀውስ ውስጥ እየከተተ ያለው የህወሃት በዘር ላይ ያተኮረ አፓርታዳዊ አገዛዝ በሥልጣን ለመቆየት እስከጠቀመው ድረስ ይህንን ረሃብ ለፖለቲካ መሣሪያ መጠቀሙ እንደማይቀር የራሱ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ በሶማሊ አስከፊ ጉዳት እያደረሰ ያለው ረሃብ ወደጎረቤት አካባቢዎች መዝለቁና ዜጎች የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ ውስጥ መግባታቸው የህወሃትን ዕድሜ እስካረዘመው ድረስ ዕልቂቱን ከማስቆም ይልቅ እንዲስፋፋ ማድረጉን ይቀጥልበት ይሆናል በማለት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡
  “የህወሃት የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ፖሊሲ፤ መቀሌን እያሳደገ ጅግጅጋን በመቅበር፣ ኦሮሚያን በማድማት ትግራይን እያለማ፣ … ይቀጥላል ማለት ዘበት ነው” በማለት ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ የክልሉ ነዋሪ “እኛ አሁን “የረሃብን ጉንፋን እየሳልን”፣ እያለቀስን፣ እየሞትን ነው፤ ነገርግን የግፍ ጽዋው የሞላ ቀን የትግራዮች የብቻ ዋይታ የበዛ እንደሚሆን ዛሬ ላይ ቆሞ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል” ይላሉ፡፡ (የመግቢያ ፎቶ: በዋርዴር ወረዳ ሕዝብ ምግብና ውሃ ሲጠብቅ :: March 25, 2017

  https : // www. youtube .com /watch?v=qxaUBqJNaVI

Leave a Reply to dergu temelese Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *