Seven things banned under Ethiopia’s state of emergency

admin

Awramba Times is a US based online journal providing up-to-date news and analysis about Ethiopia email us: [email protected]

You may also like...

4 Responses

 1. Kolonel demeke says:

  ዋናው ዐዋጅ 31 አንቀጾች አሉት፡፡
  አወጁ ያላካተታቸው ተጨማሪ አንቀፆች ከአሰፋ ዳሞቴ የተወሰደ።

  አንቀጽ 32.
  የሕዝቡን ደኅንነትና ፀጥታ ለመጠበቅ ሲባል ማንኛውም ዜጋ በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ውስጥ ስለምንም ነገር ማሰብ፣ ህልም ማለም፣ መቀባዠር፣ መቃዠትና በዕንቅፍ ልብ ማውራት የተከለከለ ነው፡፡

  አንቀጽ 33.
  ህገ መንግሥታችንን ከመጥፎ የመኪና አነዳድ ለመከላከል ሲባል ማንኛውም አሽከርካሪ መኪና ውስጥ ገብቶ ሲያሽከረክር ወደግራም ሆነ ወደ ቀኝ መታጠፍ፣ ወደቀኝም ሆነ ወደግራ ፍሬቻ ማሣየት፣ በኋላ ማርሽ የኋሊት መሄድ ወይም በፊት ማርሽ ወደፊት መንዳት፣ እስፖኪዮ መመልከት፣ ነዳጅ መቅዳት፣ ዘይት መለወጥ፣ መኪናን ላባጆ ማስገባት፣ ለሰው ሊፍት መስጠት፣ ቤተሰብ መጫን ወዘተ፣ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

  አንቀጽ 34.
  ሀገርንና ትውልድን ከሽብር ጥቃት ለመከላከል ሲባል ይህ ዐዋጅ ተግባራዊ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ አራስ ሕጻናትም ጭምር ማንኛውም ለአቅመ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የደረሰ ዜጋ ፀሐይ መሞቅ፣ አየር መተንፈስ፣ ውኃ መጠጣት፣ መፀዳጃ ቤት መሄድ፣ ሰውነቱን ማከክ፣ ንፍጡን መናፈጥ፣ ምግብ ጠግቦ መብላት፣ ሰላምታ መለዋወጥ፣ የሕወሓታውያንን ህንጻና መኪና ማየት፣ ወደነሱም ማፍጠጥ፣ ከሣሎን ወደ ጓዳ ወይም ከመኝታ ቤት ወደ ሣሎን መንቀሳቀስና ከኮማድ ፖስት ኃላፊዎች ፈቃድ ሳያገኙ ከቤተዘመድም ሆነ ከጓደኛ ገንዘብ መበደር ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ እነዚህን ሲያደርግ የሚገኝ ተሃድሶ ተሰጥቶት ለስድስት ወር ከርቸሌ ይወርዳል፡፡

  አንቀጽ 35.
  ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ታማሚን ለመጠየቅ ወይም የሞተን ለመቅበር ሲሰባሰቡ ህገ መንግሥታቸውንና በመቶ ፐርሰንት የመረጡትን ዴሞክራሲያዊ መንግሥት እንዳያሙ ሲባል በነዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ በተፈጥሮ በሽታም ሆነ በድንገተኛ አደጋ መታመምም ሆነ መሞት የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን የዜጎች መሞት በግድ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ወቅት ከሕወሓቶች በስተቀር ማንኛውም ዜጋ አጋዚና የመከላከያ ሠራዊት በሚገኙባቸው አካባቢዎች በቡድንም ይሁን በግል በመቅረብ በጅምላም ሆነ በችርቻሮ የተፈለገውን ያህል የሞት መጠን መቀበል እንደሚቻል ኮማንድ ፖስቱ በደስታ ይገልጻል፡፡(የጥይት ግን ይከፈላል)

  አንቀጽ 36.
  አካባቢን ከሁከት ለመታደግና ህገ መንግሥቱን በኃይል ከሚንዱ አሸባሪዎች ለመከላል ሲባል በዐዋጁ ጊዜ ውስጥ ማንም ዜጋ በምንም ምክንያት ጮክ ብሎም ይሁን በለኆሳስ መሣቅም ይሁን ማልቀስ፣ “እሰይ!” በማለትም ይሁን ”ውይ!”፣ “ኡፍ” በሚልም ይሁን “ኣ!ኣ!” የውስጥ ስሜቱን በገሃድና በኅቡዕ መግለጽ የተከለከለ ነው፡፡ የቤት አከራዮችም የተከራዮችን ሣቅና ልቅሶ መጠን በመቆጣጠር ከጣራ በላይ የሚስቁትንና ስቅስቅ ብለው የሚያለቅሱትን በመለየት ለሚቀርባቸው የቀበሌ አስተዳደር ጠቁሞ እርምጃ አለማስወሰድ የተከለከለ ነው፡፡

  አንቀጽ 36.
  በለጋሽና አበዳሪ ሀገሮች ሕዝባዊ የእምቢተኝነት ዐመፅ ምክንያት መንግሥት ያጋጠመውን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ ሲባል በነዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ሚስት ከባል ወይም ባል ከሚስት ለሚያገኙት ለእያንዳንዱ ፆታዊ እርካታ ብር አንድ መቶ ለመንግሥት ገቢ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን በዚህ ግንኙነታቸው ውስጥ ግን ጽንስ መቋጠር ወይም ማስቋጠር በጥብቅ የተከለከለ ነው፤ ለእርግዝና ቁጥጥሩ ቤተሰብ መምሪያ፣ ጤና ጥበቃና መከላከያ ሚኒስቴር በትብብር እንዲሠሩ በኮማንድ ፖስቱ ታዘዋል – ለትውልድ ማምከኛም በጀት ተይዞላቸዋል፡፡ ባገራችን ያለው የመንግሥትና የሕዝብ መተማመን ክፉኛ እየቀነሰ በመምጣቱ ሳቢያ ሕዝቮችና ብሔር ብሔረ ሰቮች መንግሥትን እንዳይሸውዱ ሲባል ይህን መሰሉን የግንኙነት መጠን መቆጣጠር የሚያስችል ባልቦላ(ቆጣሪ) ከፈረንሣይና ከጣሊያን በዕርዳታ በማስመጣት በያንዳንዱ ዜጋ ጭን ውስጥ ለመግጠም መንግሥት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ኮማንድ ፖስቱ ቁጭትና እልህ በተሞላት ደስታ ይገልጻል፡፡ ይህ መመሪያ የማይመለከታቸው ከ10 ዓመት ዕድሜ በታችና ከ110 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ዜጎችን ብቻ ነው፡፡ (ስለዚህ የቀድሞውን “ፕሬዝደንት” አቶ መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስን አይመለከትም ማለት ነው?)

  አንቀጽ 37.
  ሰሜን ሸዋ አካባቢ ግዳጅ ላይ እያለ የተሰዋው ሃምሣ አለቃ ደሳለኝ የተባለ የሕወሓት ዕቃ ተሸካሚ አህያ “ስም አስጠሪ ልጅ ሳይተካ ተሰዋ!” ብሎ በዚህ ሰማዕት ላይ ማላገጥ የተከለከለ ነው፡፡ እሱን የሚያስከነዳ አንድ ዐይና ጠብደል ስናር አህያ ተክቶ አልፏልና ዘሩ ባለመቋረጡ የመለስ ራዕይ የተመሰገነ ይሁን፡፡ (አብረን ይቺን መፈክር እንበል – “የመለስ ራዕይ በአህዮቻችን ግቡን ይመታል!” – “ይመታል!”)….

  አንቀጽ 38.
  የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ ለመጠበቅ ሲባል በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ማንም ዜጋ የፈለገውን መልበስ የተከለከለ ነው – ሞቀኝ በረደኝ ሳይባል መንግሥት በዝርዝር መመሪያዎች በቀጣይ የሚያወጣቸውን የልብስ ዓይነቶችና የአለባበስ ፋሽኖች አለመከተል የተከለከለ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ለምሣሌ ቀይ ፓንት ወይም ቢጫ ካናቴራ ወይም አረንጓዴ ኮፍያ ማድረግ መንግሥትን ስለሚያስደነብር በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

  አንቀጽ 39.
  ህገ መንግሥታችንን በኃይል ሊንድ ስለሚችል በዐዋጁ ጊዜ ውስጥ ዕቁብና ፅዋ ማኅበር መጠጣት፣ በዕድር ቤቶች መሰባሰብ፣ ከሦስት ወር ያለፈው የተረገዘን ጽንስ ጨምሮ ከአንድ ሰው በላይ ከቤት ውጭ መሰብሰብ ወይም ቆሞ መገኘት፣ መጠጥ ቤት መግባት፣ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ወይም በሌላ ቦታ የሆቴል ቤትን የምግብ ዝርዝር ጠቋሚ ሜኑ ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ጽፍሑ/መጽሐፍ ማንበብ … የተከለከለ ነው፡፡

  አንቀጽ 40.
  “በደህና እንዳዋልከኝ በደህና አሳድረኝ” ከሚል የግል ጸሎት ውጪ የዘወትር ጸሎትንና ውዳሤ ማርያምን ጨምሮ ማንም ዜጋ ምንም ዓይነት የምህላና የምልጃ ጸሎት በዚህ የዐዋጅ ጊዜ ውስጥ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ሀገር ሰላም ስለሆነች “ሀገረ ኢትዮጵያን ሰላም አድርግልን፤ የቀድሞ አንድነቷን መልስልን” የሚለውን የጠባቦችና የትምክህተኞች ጸሎት ማድረስና በቅዳሤም ይሁን በሌላ ጸሎት ላይ “እግዚኦ መሓረነ…” ብሎ በዜማም ይሁን በዕዝል ማመልጠን ወይ መጸለይ በጥብቅ የተከለከለ ነው – (ዋልሽ! እዚያ የሾምናቸው ልጆቻችን አሣርሽን ያበሉሻል)፡፡

  አንቀጽ 41.
  በኢ.ኦ.ቤ/ክርስቲያን የማሣረጊያ ጸሎቶች ውስጥ የጠቅላይ ሚንስትራችንን የአቶ መለስ ዜናዊንና የዶክተር አባ ጳውሎስን ስም ከብፁዕ አባታችን ከአቡነ ማትያስ ስም ጋር አለማንሣት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

  አንቀጽ 42.
  የህዳሴያችንንና የህገ መንግሥታችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ማንኛውም ዜጋ ኢቢሲን ጨምሮ ሁሉንም የኢትዮጵያ ሚዲያዎች መመልከት፣ ማዳመጥና ማንበብ አለበት፤ ከዚህ በተያያዘ ቢቢሲንና ቪኦኤን ጨምሮ ምንም ዓይነት የውጭ ማስሚዲያ መከታተል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

 2. Tiger says:

  Kolonel demeke, ብዙ ጊዜ ሰውን አስቃለው ባዩች .. ትንሽ ሰውን ፈገግ ለማስደረግ ማመልከቻ ደብዳቤ ይመስል ገፁን ሙሉ መቸክቸክህ : የአንተን ዝባዝንኬ ሳነብ :ወርቃማ ሰአቴን አቃጠልኩት : አስቡት ፊስቡክ ባይዘጋ ኖሮ : በእንደነዚ አይነቶች ትርካምርኪ ተጨናንቃ ነበር .

  • Kolonel demeke says:

   አቶ ታይገር
   አንተ በቁም ነገር ያወጣሀቸው ህጎችና፣ አሰፋ ዳሞቴ ያወጣቸው ሀጎች ስለተቀራረቡብኝ ፣ለግንዛቤ፣ለማወዳደር ነው ። ግን በደንብ ተመልከታቸው አንድ ባይሆኑም ይቀራረባሉ እንጂ ከማሳቅ ጋ ግንኙነት የለውም።

 3. Sirgut says:

  አሁን ያለዉን ጥያቄ በአንክሮ ከየነዉ ምናልባት በትክክለኛዉ ቋንቋ ትርጉም ከሰጠነዉ፡፡
  1. ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ጥያዎች!
  2. ኦሮሚኛ ከአማሪኛ ጋር የፌድራል የሥራ ቋንቋ ይሁን
  2. ፍትሃዊ የስልጣን ክፍፍል ጥያቄዎች!
  3. የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም (ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ ና ማህበራዊ) በአ.አ ጉዳይ ላይ !
  4. የፌድሬሽኑ መስራች ና አባል ዘጠኙ ክልሎች የጎንዮሽ ግንኙነት ምን መሆን አለበት
  5. በርግጥ ጎንደሬዎች ያነሱት ጉዳይ በህግ ዓይንም አወዛጋቢ ልሆን ይችላል፡፡ ድንበራችን ተካዜ ነዉ የሚለዉ ነገር ትግሬዎችን ባይተዋር እንዳያደርገቸዉ …ቀጥሎኮ ያለዉ የኢሣያስ ሀገር ነዉ፡ ወይስ ምንድነዉ ነገሩ፡፡
  6. የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነዉ፡ ዘላለማዊ ክብር ለጎንደር ልጆች …ከሚበለዉ በላይ ኢትዮጵያን አንድ አደረጓት፡፡

  ምንም ይሁን ምን ሀገራችን ኢትዮጵያ በ100 ምናምን ዓመቷ አይታ የማታዉቀዉን ህዝባዊ ማዕባል መንግስትን እንደ አዉሎ ንፈስ ስያንሣፍፈዉ እያየን. The commanding and demanding society is good sign of maturing democracy, the government response oughnot be undemocratic like what we have experienced during the past regimes. Right!

  እየኖርን ያለነዉ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን …ከግዜ እየዘመን መሄድ ነዉ እንጂ እንደ ደብተራ አንዱኑ መጽሃፍ ደጋግመን እያናበብን ብንዉል …ትርፉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ … ሀገር ማለት እናት ነች፤ ሀገር ማለት አባት ነዉ፡፡ አባት ና እናቱን ማንም አይጠለም፡፡ አንድ ሰዉ I love Tigray/Oromia ስላለ ኢትዮጵያን ጠልተዋል ብለን መደምደም በጣም ስህተት ይመስለኛል፡፡ Generalization is not good! Some of us say I love Ethipia yet hate certain particular etnic group that clearly define their identity in light of their language and culture. What is Ethiopia without its people-defined by its language and culture? so Ethiopia forever with its people!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *